ቅድስት እንባ መሪና
የቅድስት እንባ መሪና እናት ማርያም ትባላለች ገናም ህጻን እያለች ነበር በሞት የተለየቻት ከዛም አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በጎ ትምህርቶችን እያስተማራት አሳደጋት በኋላም ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ አጋብቷት እሱ ወደ መነኮሳት መኖሪያ ሄዶ ሊኖር እንደ ወደደ ሲነግራት እጅግ አልቅሳ "አባቴ ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ማጥፋት እንዴት ይሆንልሃል?" አለችው አባቷም እኔ የምሄደው ወደ ወንድ መነኮሳት ነው አንቺ ደግሞ ሴት ነሽ አያስገቡሽም ሲላት እንደ ወንድ ሱሪ አድርጌ ጸጉሬን ተቆርጬ ወንድ መስዬ ካንተ ጋር እሄዳለው አለችውና ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሽጠው እና ለደሃ መጽውተው ተያይዘው ገዳም ይገባሉ:: በዚአም ገዳም እጅግ እየተጋደሉ ኖሩ በኋላም አባቷ በጸና ታመመና አበምኔቱን አስጠርቶ ልጄን አደራ በምንም መልኩ ከገዳም እንዳይወጣብኝ ይልና አበምኔቱን አደራ ይለውና ያርፋል፡፡ ቅድስት እንባ መሪናም ተጋድሎዋን ከቀድሞ እጅግ አብዝታ ትተጋ ጀመር ከረጅም ግዜ በኋላም የገዳሙ መነኮሳት ይሄ መነኩሴ ከኛ ጋር ለምንድን ነው ከገዳም ውጪ ለተልዕኮ የማይወጣው እያሉ አበ ምኔቱን አስጨነቁት በኋላም አበ ምኔቱ ከመነኮሳቱ ጋር አብሮ ይሰዳት ጀመር የሚሄዱትም የገዳሙን ምግብ በየግዜው ከሚሰበስብላቸው አንድ ሰውዬ ቤት ነበር እንዳስለመዱት በየግዜው ሲሄዱ አንድ ቀን ምግቡን የሚሰጣቸው ሰውዬ አንዲት ልጅ አለችውና ጎረቤት የሆነ አንድ ጎረምሳ ተደብቆ ገብቶ የሰውዬውን ልጅ ድንግልናዋን ያፈርሳል በኋላም አባትሽ ማነው እንዲህ ያደረገሽ ብሎ ከጠየቀሽ እንባ መሪና ነው በይ ይላትና ይሄዳል፡፡ ልጅቷም ታረግዛለች አባትየውም ከማን እንዳረገዘች ሲጠይቃት ከመነኩሴው ከእንባ መሪና ነው አለችው ከዛም ያ ሰውዬ ወደ ገዳሙ ይመጣና በአደባባይ መነኮሳቱን ይረግማቸው ጀመር ከዛም አበ ምኔቱ መጣና ምን ሆነህ ነው ቢለው ልጄን ያንተ መነኩሴ ደፈረብኝ ሲለው ታድያ ባንድ ሰው ጥፋት እነዚንህ ሁሉ ቅዱሳን ለምን በአደባባይ ትረግማለህ አለውና እንባመሪናን አስጠራት መጣችና አቤት አባቴ ስትል ሁሉም ይሰድቧት ጀመር ለምን እንደሚሰድቧት ባታቅም ሰይጣን የሰራባት ነገር እንዳለ ገብቷት ዝም አለች በኋላም ነገሩን ነገሯት እና አበ ምኔቱ "እንባ መሪና ይህ የመነኩሴ አይደለም የአለማውያንም ባህሪ አይደለም የሰይጣን እንጂ ይህን ለምን ሆነ?"ብሎ ቢጠይቃት እሷም አባቴ ይቅር በለኝ ወጣትነት አታሎኝ ነው አባቴ ይቅር በለኝ ብላ አበ ምኔቱ እግር ስር ወደቀች በኋላም አበ ምኔቱ ከገዳሙ አባረራት እና ከገዳሙ ውጪ ሆና ትጋደል ጀመር፡፡ ያቺም ልጅ ስትወልድ አባቷ ልጁን አምጥቶ ለእንባ መሪና ሰጣት እንባ መሪናም ለልጁ የሚሆን ወተት እና ምግብ በአካባቢው ያሉትን እረኞች እየለመነች አሳደገችው ከ3 አመት በኋላም መነኮሳቱ አበ ምኔቱን ለመኑት ባይሆን ከባድ ቀኖና ይሰጠውና ወደ ገዳም ይግባ አሉት አበ ምኔቱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከባድ ቀኖና ሰጣት እና ስትጨርስ ወደ ገዳሙ ተቀላቀለች ከዛም ገዳሙ ውስጥ ያሉትን ከባድ ስራዎች ያሰሯት ጀመር የመነኮሳቱን ቤት ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳም ውጪ አውጥታ ትጥላለች ያም የተወለደው ልጅ አድጎ እዛው መነኮሰ 40 አመትም ከተፈጸመ በኋላ ቅድስት እንባ መሪና 3ቀን ታማ አረፈች የገዳሙ መነኮሳት ደውል ደውለው ተሰበሰቡ ሊገንዟትም ፈልገው ልብሷን ሲያወልቁት ሴት ሆና ሲያገኟት እጅግ አዝነው አበ ምኔቱን አስጠሩት አበ ምኔቱም የተፈጠረውን አይቶ እጅግ አዝኖ አለቀሰ ያለበደሏ የሰጣትን ቀኖና እና የተናገራትን ተግሳጽ እያሰበ አምርሮ ያለቅስ ጀመር፡፡ ያን የልጅቷንም አባት አስጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገረው ከዛም በድኗን ተሸክመው አቤቱ ይቅር በለኝ እያሉ ዋሉ ማምሻውን ላይ የቅድስት እንባ መሪና አስክሬን "እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ" ሲላቸው አውርደዋት በታላቅ ክብር ከስጋዋም ተባርከው ቀበሯት ከመቃብሯም እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ጻድቅ ጸሎት ይማረን፡፡
No comments:
Post a Comment