1, አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ለምን ምስጢር ተባሉ? 2, ለምን አዕማድ(ምሰሶ) ተባሉ?
አምድ ማለት ምሰሶ ማለት ሲሆን ቤት እንዳይዘም ሚዛኑን እና ልኩን ጠብቆ እንዲቆም የሚያደርግ ነው።
አዕማድ ስንልም ምሰሶዎች (ለብዙ )ማለት ነው።
ቤት በአምድ እንደሚጸና ሃይማኖትም በእነዚህ አዕማደ ምሥጢራት መሠረትነት ይፀናልና ነው፡፡
ምሥጢር ስንል በሚታዩ ምሳሌዎች የማይታየውን የሃይማኖት ምሥጢር መረዳት፤ በሚታይ አገልግሎት
የማይታይ ጸጋ ማግኘት ማለት ነው።
ማለትም አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት
★በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
·★ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ ነው፡፡
★በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋ ያስገኛልና ነው፡፡
# ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡
ምሥጢር ስንል በሚታዩ ምሳሌዎች የማይታየውን የሃይማኖት ምሥጢር መረዳት፤ በሚታይ አገልግሎት
የማይታይ ጸጋ ማግኘት ማለት ነው።
ማለትም አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት
★በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
·★ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ ነው፡፡
★በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋ ያስገኛልና ነው፡፡
# ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡
★የፈጣሪ ምሥጢር ፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ ከ እስከ የሌለው ምሥጢርም ይባላል፡፡
★የፍጡራን ምሥጢር ፡- በጊዜ ሂደት የሚገለጥ (የሚታወቅ) ነው፡፡ የሰውና የመላእክት
ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
ምሥጢረ ሥላሴ
ሥላሴ ሥንል ልዩ ሶስትነት ልዩ አንድነት ማለት ነው፡፡
የሥላሴ ሦስትነት በአካል ፣በስምና በግብር ነው፡፡
#የስም
የስም ሦስትነት
አብ ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡አንዳቸው በሌላው ስም አይጠሩም፡፡ይህ ስማቸው ግን ግብራቸውን የሚገልጥ ነው፡፡
‹‹ ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዝሙራቴ አድርጓቸው››ማቴ28፤19
#የግብር
የግብር ሦስትነት
በግብር አብ ወላዲና አስራጺ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስም ሠራጺ/ከአብ የወጣ/ ነው፡፡
ሦስትነት፦ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ፍጹም አካል፣ፍጹም ገጽ፣ፍጹም
#የአካል
የአካል መልክ አላቸው ማለት፡፡ ይህ አካል ዝርው (ብትን) ያልሆነ ረቂቅ መንፈሳዊ አካል ነው፡፡
አብ ወልድን ወለደ ስንል ከአካሉ ከባሕርይው ፤ አስገኘው ማለት ነው፡፡
ወልድ ከአብ ተወለደ ስንል አብን አክሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
አብ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸው ማለት ፤ ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለት ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸ ስንል አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
የሚከተሉትን # ጥቅሶች ስንመለከት የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት ያሳያሉ፡፡
ዘፍ 1፥26 እግዚአብሔርም አለ፦ስውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር።
እግዚአብሔርም አለ ብሎ አንድነቱን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር ሲል ደግሞ
ብዛትን ( ሦስትነት ) ይገልጻል።
ዘፍ 3፥22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ
እንደ አንዱ ሆነ። ከእኛ የሚለውና እንደ አንዱ የሚለው እግዚአብሔር ከአንድ በላይ እንደሆነ
የጠቆመን ናቸው።
ዘፍ 11፥7 ኑ፥ እንውርድ አንዱ የአንዱን እንዳይስማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
ኑ የሚለው ቃል የሚያስርዳን አንዱ አካል ሌሎችን ሁለትና
ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል መጥራቱን ነው።
ዘፍ 18፥1-15 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር
በመምሬ አድባር ዛፍ ተገለጠለት። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት
ስዎች በፊቱ ቆመው አየባቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተንሥቶ እሮጠ ፥ወደ
ምድርም ስገደ፥እንድህም አለ፥በፍትህስ ሞገስን አግንቼ እንደ ሆነ
ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ።
ኢሳ 6፥1-3ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ
ተሞልታለች እያለ ይጮኸ ነበር። አንዱ ቅዱስ ለአብ ሁለተኛው ቅዱስ ለወልድ ሦስተኛው
ቅዱስ ለመንፈስቅዱስ መሆኑን ልብ እንበል። ይህንን
በድጋሜ ራዕይ 4፥8እናገኘዋለን።
ኢሳ 48፥16... አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እና መንፈሱ ልከውኛል።
ማቴ 3፥16 ኢየሱስም ከተቀመጠ በኃላ ወድያው ከውሃው ወጣ፤እነሆም፤ስማያት
ተከፈቱ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲመጣ አየ፤
እነሆም፥ድምጽ ከስማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ
የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
ማቴ 28፥19 እንግድህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድን በመንፈስቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዝሙር አድርጓቸው፤እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድርስ ሁልጊዜ
ከእናንተ ጋር ነኝ።
ሉቃ 1፥35 መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑል ኃይል ይጽልልሻል ስለዚህ
ደግሞ የሚወለደው የእግዚአብሔር ቅዱስ ልጅ ይባላል።
ዮሐ 14 ፥ 25 ከእናንተ ዘንድ ሲኖር ይህን ነግሬአቹኃለሁ፤ አብ በስሜ የሚልከውን ግን
መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔ
መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔ
የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
1ኛ ቆሮ 12፥3 ስለዝህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተርገመ ነው
የሚል እንደሌለ ፥ በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ
ነው ሊል እንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
2ኛ ቆሮ 13፥14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሔር ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም
ህብርት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
# የሥላሴ አንድነት
በመለኮት፣በአገዛዝ፣በሥልጣን፣ይህንን ዓለም ፈጥሮ በማሳለፍ ፣በፈቃድ እና
በመሳሰሉት ነገሮች አንድ ናቸው፡፡
# በህልውና አንድ ናቸው ማለት
★አብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው/ይኖራል/፣
★ወልድም በአብና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ህልው ነው፣
★መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ውስጥ ህልው ነው፡ዮሐ14፤8-11
★
አንድ ናቸው ስንል በመፍጠር፣በመስጠት፣በመንሳት፣በማዳን፣በመግደል፣በ
#
#በመለኮት
በመለኮት
ማጽደቅ፣በመኮነን ይህንን በመሳሰሉ ሁሉ አንድ ናቸው ማለት ነው፡፡
★ሥላሴ
በመባል አንድ ናቸው፡፡ ዘዳ 6፤4 2ኛቆሮ13፤14; የሐዋ20፤28;
#
#እግዚአብሔር
እግዚአብሔር
ሐዋ5፤3-6;
የሥላሴን # አንድነትና # ሶስትነት በምሳሌ
➊የሰው ነፍስ
ኩነት ወይም ከዊን ማለት ሁኔታ ወይም መሆን ማለት
ሲሆን ፣ ይህም በሰው ነፍስ ምሳሌ ይገለጻል ። ነፍስ አንዲት ስትሆን ሶስት ባህርያት
(ኩነታት ) አሏት ፤
★እነሱም ፤ ልብ (ማሰብ ) ፤ ቃል (መናገር ) ፤ እስትንፋስ (ሕይወት ) ናቸው ። ከሶስቱ
ባህር ያት
አንዱ ከተጓደለ ነፍስ የሚለውን ስም ልታገኝ አትችልም ።
★ይኸውም አብ በልብ (ማሰብ ) ፣ ወልድ በቃል (መናገር ) ፣ መን ፈስ ቅዱስ በእስትፋስ
(ሕይወት ) ሲሆን አብ ለራሱ ልብ ሆኖ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው ። ወልድም
ለራሱ ቃል ሆኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው ። መንፈስ ቅዱስም ለራሱ ሕይወት
ሆኖ ለአብና ለወልድ ሕይወታቸው ነው ። በ እግዚአብሔርነቱ ፤ ልብ ፣ ቃል፣ ሕይወት አለ ።
★
ሶስት ባህርያት ቢኖሯትም አንድ እንደምትባል እግዚአብሔርም በስም፣ በአካል፣
#
#ነፍስ
ነፍስ
በግብር ሶስት ቢባል አንድ አምላክ እንጅ ሶስት አማልክት አይባልም ። ዘዳ 6 ፥4 ፡ ሚል 2፥
10::
➋ፀሀይ
ክበብ ብርሃን ሙቀት አላት ። በክበቧ አብ ፣በብርሃኗ ወልድ ፣ በሙቀቷ መንፈስ ቅዱስ
ምሳሌ
ሆነው ቀርበዋል ። ፀሀይ ሶስት ሁኔታዎች ሲኖሯት አንድ እንደሆነች እግዚአብሔርም አንድ
ሲሆን ሶስት ፤ ሶስት ሲሆን አንድ አምላክ ነው ።
➌ውሃ
ይዘት፣ እርጥበት ፣ ቅዝቃዜ አለው ። በይዘቱ አብ ፣ በእርጥበቱ ወልድ ፣ በቅዝቃዜው መንፈስ
ቅዱስ ይመሰላሉ ። ውሃ አንድ እንደሆነ እግዚአብሔርም አንድ ሲሆን ሶስት ፤ ሶስት ሲሆን
አንድ አምላክ ነው ።
ሌሎቹም በምሳሌነትየሚቀርቡ ፍጥረታት አሉ ። ነገር ግን ሁሉም በምሳሌነታቸው
ለማስተማር እንጅ የአምላክን : ባህርይ # የፍጡር ባህርይ ሊያስረዳ አይችልም ።
#
No comments:
Post a Comment